127ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል “ጀግንነት፡ አይበገሬነት እና ጽናት” በሚል መሪ-ቃል በኤምባሲው በድምቀት ተከብሯል።
ክቡር አምባሳደር ስለሺ በቀለ በእለቱ እንደገለጹት “የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ ድንበር አልፎ ለአፍሪካ ብሎም ለመላው አለም የነጻነት ጎህን የቀደደ፣የለኮሰ፣ የአልገዛም፣ አልበገርም፣ የእምቢ ለሃገሬ ባይነት መንፈስን ለመላው ጭቁን ህዝቦች ያጎናጸፈ አቻ የሌለው የብቃት ምልክት ነው።”“የአድዋ ጀግኖች ዘር፣ ቀለም፣ የፖለቲካ ልዩነት፣ አካባቢ፣ ጥቅም እና ሌላም ምክንያት ሳይጠቅሱ ለአገር እንደተመሙት ሁሉ በአሜሪካ የሚገኘው ዳያስፖራ አገራችሁ ጥሪ ባደረገችባቸው ወቅቶች ሁሉ […]
