የሕዝብን ጥያቄዎች “ከጎዳና ወደ ፓርላማ” የሚወስድ ምርጫ! (April 25, 2021)
የዘንድሮው ምርጫ የዘመናት ቋጠሮዎች የሚፈቱበት ቁልፍ እንደሆነ መዘንጋት ሞኝነት ነው፡፡ በሀገራችን ለበርካታ ዓመታት የሕዝቦችን ጥያቄ ወደ ተገቢው የዴሞክራሲ ባሕል መንገድ ማስገባት አልተቻለም ነበር። ጉዳዩን ወደኋላ አርዝመን ካየነው ምናልባትም ከታኅሳሱ ግርግርና ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ የሕዝባችን የፖለቲካ ጥያቄዎች በዋናነት የሚንጸባረቁት አንድም በጎዳና ላይ ዐመጽ፣ ሁለትም በጦር መሣሪያ አማካኝነት ነበር። ሁለቱም መንገዶች እጅግ ኋላቀርና አውዳሚዎች እንደ ነበሩ እስኪበቃን […]
