” የመጪውን ትውልድ በአባይ ውሃ የመልማት መብት የሚጋፉ አቋሞችን ኢትዮጵያ አትቀበልም” – አምባሳደር ስለሺ በቀለ
(ታኀሣሥ 10 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ):-የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ(ዶ/ር)፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ዙሪያ ከግብፅና ሱዳን ጋር በተደረገው አራተኛ ዙር ድርድር ዙሪያ በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።ኢንጅነር ስለሽ በቀለ በመግለጫቸው፣የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)ና የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ሐምሌ 2015 ዓ.ም የሰጡትን አቅጣጫ ተከትሎ፣ በኢትዮጵያ፣ ግብፅና […]
