በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያና የዳያስፖራ ሁለንተናዊ ተሳትፎን አስመልክቶ በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው የሚኖሩ ዳያስፖራዎችን ያሳተፈ የውይይት መድረክ በዋሺንግተን ዲሲ የኤፌዲሪ ኤምባሲ በሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓም ተካሄደ።
በውይይት መድረኩ ላይ ክቡር የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሰደር አርጋ፣ በዋሺንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ክቡር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ እና በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶር መሀመድ እንድሪስ የሚመራው የልኡካን ቡድን አወያይነት በኤምባሲው ግቢ ተከናውኗል።ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ በእለቱ ባደረጉት ንግግር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በጋራ በመሆን ሳይከፋፈሉ […]
