የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ መጋቢት 20/2015(ኢዜአ)፦የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሀገራዊና ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።ስምምነቱንም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ታዜር ገብረእግዚአብሔርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተፈራርመዋል።አቶ ታዜር በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ከዕለታዊ ስራዎች ጀምሮ በስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር […]
