ክቡር አምሳሳደር ስለሺ በቀለ በአሜሪካ ከሚገኙ ከ36 በላይ የዳያስፖራ አደረጃጀት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ሰኔ 8/2015 ዓ.ም ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱም በአገራችን ዘላቂ ሰላም ለመገንባት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች፣ የገጠሙ ፈተናዎችና መፍትሄዎቻቸው፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከቤተ-እምነቶች እና መኖሪ ቤቶች ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች፣ በአገራችን ሰላምና አንድነት የዳያስፖራው ተሳትፎ፣ በሁለትዮሽ ግንኙነትና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። አምባሳደር ስለሺ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት በአገራችን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን መንግስት ሁሉን አቀፍ […]
