ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር ሼህ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ የመሩት ልኡካን ቡድንን በዛሬው እለት ሐምሌ 18 ቀን 2015 ዓም በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አካሂደዋል።
ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ በእለቱ ባደረጉት ንግግር የልኡካን ቡድኑ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ማለትም ዲኤምቪ ፣ ሚኒሶታ ፣ ዋሺንግተን ሲያትል እና ቴክሳስ ሂውስተን ያደረገዉ የስራ ጉብኝት የመጣበትን አላማ ለማሳካት ከፍተኛ ፋይዳ ያለዉ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የሚገኙ የኢትዮጵያ የሙስሊም ዳያስፖራ ተቋማት ፣ አደረጃጀቶች እና ማህበረሰብ በሀገራቸዉ ጉዳይ ላይ ከአሁን በፊት ያደርጉ የነበረዉን አስተዋጽኦ እና […]
